|
ኢ.ኤ.ኤስ. ሶፍትዌር ቴክኖሎጂስ የደንበኞቹን የአይ.ሲ.ቲ. (ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ) ፍላጎቶች ለማሟላት የተቋቋመ በምእራቡ አለም ተሞክረው ውጤታማነታቸው የተረጋገጡ ዘመናዊ አሰራሮችንና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን የሚከተል ድርጅት ነው። ከአገልግሎቶቻችን ጥቂቶቹ ፦ አጠቃላይ ማማከር ፤ፕሮጄክቶችን መቅረጽ እና መከታተል፤ የሶፍትዌር ዴቬሎፕመንት ስራዎችን ከሃገር ውስጥ እንዲሁም ኖርዌይ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስራቤት ጋር በመተባበር በአለም አቀፍ ደረጃ መወጣት፤ የግራፊክ ዲዛይን እና ድረ ገጽ ስራዎች መስራት፤ የኢንተርኔት ዶሜይን ማስመዝገብ እና መከታተል፤ የሰርቨር ቦታ ማከራየት ፤ የኮምፒውተር መረቦች(ኔትወርክ) የተመለከት ምክር፤ ዲዛይን እና መስመር መዘርጋት እንዲሁም የኮምፕውተር ጥገናዎችን ማከናወን ናቸው።
ግባችን:
- ለተከበሩ ደንበኞቻችን ጥራት ያለው የአይ.ሲ.ቲ. አገልግሎቶችን መስጠት
- ለአጋሮቻችን አስተማማኝ የአይ.ሲ.ቲ. አገልግሎቶቸን አቅራቢ በመሆን ለደንበኞቻቸው የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ማጎልበት
- አለም አቀፍ የሶፍትዌር ስራዎችን በመስራት ኢትዮጵያ የድንበር ዘለል ስራ(Outsourcing) ተጠቃሚ እንድትሆን ፈር መቅደድ
ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው እሴቶች:
- የደንበኞቻችን እርካታ
- የአገልግሎታችን ጥራት
- ፕሮፌሽናል አገልግሎት አሰጣጥና አጠቃላይ ዘመናዊ አሰራር
|
|